በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወጥታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ምስጋና እናቀርባለን
ነፃነት በነፃ እንደማይገኝ አውቃችሁ ለሀገራችሁ እና ለህዝባችሁ መስዋእትነት ለመክፈል ለቆረጣችሁና ፍርሀትን ለሰበራችሁ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች በመላው አለም ተበትነን የምንገኝ የኢትዮጵያ ወቅታዊ መወያያ መድረክ (ECADF) ታዳሚዎች አድናቆታችንና ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በተጨማሪም ይህንን ህዝባዊ ሰልፍ ለጠራው እና ላስተባበረው የሰማያዊ ፓርቲ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ለደገፉና ለተባበሩ የፖለቲካና ሲቪክ ድርጅቶች፣ በማህበራዊ መገናኛ መረቦች ስትቀሰቅሱና ስታስተባብሩ ለነበራችሁ ለውጥ አራማጆች ያለንን አድናቆት ልናስተላልፍ እንወዳለን።

እንደተለመደው እኛ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ (ECADF) የምንሰባሰብ ኢትዮጵያውያን ምንግዜም ከለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ጎን ተሰልፈን የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደምንቀጥል በድጋሜ ቃል-እንገባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ
Ethiopian Current Affairs Discussion Forum (ECADF)
Ethiopian Current Affairs Discussion Forum (ECADF)
posted by Mandefro Mengistu
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar