
ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በፈረንጆች አቆጣጠር ጃንዋሪ 13/2013ዓ.ም ለ4 ሰዓታት ያህል የፈጀ የተሌ ኮንፈረስ ስብሰባ
አድርጓል። በተካሄደው ስብሰባ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎቻችን ላይ እያደረሰ ያለው የሰብኣዊ መብት
ጥሰት፣ እንግልት፣ ወከባና እስር በመሳሰሉት አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው ተወያይቷል። በውይይቱ መደምደምያም
ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ ለገዢው ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው፣ ለፍትሕና ለሰብኣዊ መብት የቆሙ ዓለም አቀፍ
ተቋማትና ታጋይ ሀይሎች፣ ለሀይማኖትና ሲቪክ ማሕበራት፣ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚከተለውን የጋራ
መግለጫና ውሳኔ አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያ በህወሓት/ኢሕአዴግ በአንድ ፈላጭ ቆራጭ ቡድናዊ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት ቀን ጀምሮ እኖሆ ሁለት አሰርተ
ዓመታት አስቆጥራለች። ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ሲወጣ ካለፈው የተሻለ የዲሞክራሲ ለውጥ ይመጣል የሚል በብዙ ሰዎች ዘንድ
የተስፋ ጭላንጭል ተጥሎለት ቢኖርም “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በኋላ ግን ተስፋ የተጣለለትን
ዲሞክራሲ ደብዛውን በማጥፋት “ከፋፍለህ፣ በሆዱ ይዘህ፣ አሸብረህ፣ አደናግረህ፣ አናቁረህና አደንዝዘህ ግዛ” የሚለውን ሌሎች
ዲክታተራዊያን መንግስታት የሚከተሉትን የጡንቻ አገዛዝ ዘይቤ የዲሞክራሲ ሽፋን በመስጠት ዘላለማዊ ስልጣናቸውን
ለማጠናክር ሲሉ በበለጠ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል።
ዛሬ ከቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላም እሳቸው የተከሉትን ጨቋኝ ስርዓትና የአፈና መዋቀር እንዳለ
በመከተል በእግዚሄር ፍቃድ ያረፉትን መሪ የሳቸው ሞት ሌሎች ተቋዋሚ ድርጅቶች ዋጋ እየከፈሉበት ይገኛሉ። በተለይም
ላለፉት 40 ዓመታት በህወሓት ሞኖፓላዊ አገዛዝ ስር ወድቆ በሆስቴጅ (ጅሆ) ተይዞ በሻዕቢያና በህወሓት መካከል አጣብቕኝ
ውስጥ ገብቶ በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኘው የትግራይ ህዝብ ከወትሮው በባሰ መልኩ የአቶ መለስ ዕረፍት ዕዳ ከፋይና ሰለባ
ተቀባይ ሆኖ ይገኛል። ሰሞኑን በተለያየ ሚዲያ ሲገለፅ እንደሰነበተ ሁሉ ከራያ እስከ ሁመራ ድረስ በተለይም “በዓረና መደረክ”
አባላት ላይ በማነጣጠር በማሰር፣ በማስፈራራት፣ ፅሕፈት ቤታቸውን በመዝጋትና በመዝረፍ፣ ልሳናቸውን በመንጠቅና የተለያየ
መሰናክል በመፍጠር ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ከፍተኛ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የህወሓት መሪዎች የራሳቸው የግል የጓሮ ንብረት አድርገው የሚቆጣጠሩትን የትግራይ ህዝብ “ቢቸግረውም ከኛ አልፎ አቤት
የሚልበት ሌላ አማራጭ መንገድ የለውም፣ ወደደም ጠላም ከኛ ቁጥጥር አያልፍም” በሚል ንቀትና ትዕቢት የተነሳ ፓለቲካዊ
መብቱ ብቻ ሳይሆን የግል ስብእናውን፣ ማህበራዊ ፋብሪኩንና ቤት ንብረቱንም ጭምር በግፍ እያፈራረሱት ይገኛሉ። ሰሞኑን
እንደተገለፀው በራያ አላማጣ ከተማ፣ በሁመራና በሌሎች የትግራይ ከተሞች የሚገኙ ወገኖቻችን ቤታቸው እየተናደና እየተፈናቀሉ
ይገኛሉ።
በዜጎች ላይ የሚፈፀመው የሰብኣዊ መብት ጥሰትና መፈናቀል በትግራይ ህዝብ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በሌሎች ክፍላተ
ሀገርም ተመሳሳይ ግፍ እየተፈፀመ ይገኛል። የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በትግራይ ላይ የጀመረውን ዘመቻ በማሀል ሀገርም
በመቀጠል በሌሎች የመድረክ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በሽብርተኝነት ስም ማሰር መደብደብና ማንገላታት አሁንም በሰፊው ስራየ
ብለው ተያይዘውታል። ከዚህም አልፈው በሀይማኖት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጣልቃ በመግባት በምእመናን ወገኖቻችን
ላይ እየተካሄደ ያለው የከፋፍለህና አናቁረህ ግዛ እርምጃ እየተባባሰ መምጣቱ ለብዙ ዜጎች አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ይገኛል።
የተከበራችሁ የተከበራችሁ ውድ ውድ ውድውድ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያውያን ሆይ ሆይ!! ሆይሆይ!! !!!!
የህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያላቸው የንቀትና የማንአለብኝነት ድርጊት በሰብኣዊ መብት ጥሰት ብቻ
የተወሰነ አይደለም። በሉዓላዊነታችን ላይ እየተዶለተ ያለው ሴራም በሀገራችን ላይ ያንጃበበ አደጋ መሆኑን ልብ ልነው ይገባል።
በተለይም በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመን ድብቅ አጀንዳ ሆኖ በሚስጢር ይሰራበት የነበረ ጉዳይ አሁን በነ በረከት ስምዖን ጋሃድ እየሆነ
መጥቷል። አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ በኤርትራውያን መድረክ ላይ ተገኝቶ የዳር ድንበርንና ባድመን በሚመለከት ተጠይቆ
“ባድመ በሕግ ለኤርትራ የተሰጠ ስለሆነ ውሳኔው ቀደም ሲልም ተቀብለናል። ለወደፊትም የኛ ያልሆነውን መሬት የኛ ነው ብለን
መከራከር አንችልም። በሕግ አኳያም ተገቢ አይደለም። ስለዚህ ባድመ የኤርትራ መሬት መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ
በማለት ሲገልፅ ስለ ባህር በር በሚመለከት ደግሞ የወደብ ጥያቄ የድሮ ህልመኞች (ኦልድ ስኩል) የሚያነሱት አጀንዳ እንጂ በዚሁ
ሰላሳ ዓመት ውስጥ ተወልዶ ያደገ ወጣት ኢትዮጵያዊ ጥያቄውም ጉዳዩም አይደለም ረስቶታል” ብለዋል። አቶ በረከት ንግግሩን
በመቀጠል “ቀድምም ቢሆን ከኤርትራ ጋር ወደ አላስፈላጊ ግጭትና ደም መፋሰስ እንድንገባ የገፋፉንና ኤርትራውያንን ከኢትዮጵያ
እንዲባረሩ ያነሳሱት ትምክህትና ጦረኛ አመለካከት ያላቸው እነ አቶ ገብሩ አስራትና እነ አቶ ስየ አብርሃ ናቸው እንጂ የኛ አካሄድና
አቋም ከመጀመሪያውም ግልፅ ነው። አሁንም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ኖርማላይዘሽን እንዲኖር እየሰራን ስለሆነ በቅርብ ጊዜ
እውን እንደሚሆን አረጋግጥላችኋለሁ” ሲል በልበ ሙሉነት ሲናገር ተሰምቷል።
በኛ አመለካከት በኢትዮጵያና በኤርትራ ወንድማማች ህዝብ መካከል በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዘላቂ ግንኙነት እንዲኖር
ከገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ መሪዎች በላይ የምንመኘውና የምናምንበትም ጉዳይ ነው። በዳር ድንበር ዙሪያ የተፈጠረው ችግርም
ሊፈታ የሚችለው ህዝብ ያልወከላቸው ከሕግ በላይ የሆኑት ጥቂት አምባ ገነን መሪዎች በጓሮ በር በሚያደርጉት የፓለቲካ ቁማር
ጫዋታና ሕገ ወጥ ሽኩት ሳይሆነ የሁለቱን ህዝቦች ይሁንታ ታክሎበት ዘላቂ ሰላምና መልካም ጉርብትና በሚያመጣ መልኩ
ሕጋዊና ርትኣዊ መድረክ ሲፈጠር ብቻ ነው የሚል ፅኑ እምነት አለን። ነገር ግን የአቶ በረከት አነጋገር ባንድ በኩል ለሰላም የቆመና
ለኤርትራ ልዩ ተቆርቋሪ በመምሰል ሌላውን በመወንጀል ከደሙ ንፁህ ነኝ የሚል ጲላጦስ ሆኖ ለመቅረብና ለመመፃደቅ ሞክሯል።
በሌላ መልኩ ደግሞ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ለሉዓላዊነታቸው የከፈሉትን አኩሪ መስዋእትነት ደማቸውና አጥንታቸው
ገና ሳይደርቅ፣ እንዲሁም በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በየጊዜው በሻዕቢያ ታጣቂዎች እየታደኑና እየታፈኑ የሚወሰዱት ዜጎቻችን
ጥብቅና የሚቆምላቸው መንግስት አጥተው የት እንደደረሱ ሳያስጨንቀው ብድግ ብሎ ብሄራዊ ጥቅማችንን የሚነካ በጥቁር ገበያ
ማሻሻጫና ለግል ዝና መጠቀሚያ ለማድረግ መሞኮር ወንጀል ከመሆኑም በላይ ሌላ ጦርነት የሚቀሰቅስና የኢትዮጵያ ህዝብ ቁስል
የሚነካ ፀብ አጫሪ ድርጊት እንደሆነ አሁንም ልብ ልንለው ይገባል እንላለን።
እነዚህንና ሌሎች አዝማሚያዎች በአንክሮ ስንመለከትም እውነት ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው? ባለቤትዋስ ማን ነው?
የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ አድርጎናል። በመሆኑም እኛ በዲያስፓራ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውራጳና በሌሎች አህጉርራት የምንገኝ
የዓረና መድረክ ደጋፊዎች ከላይ በጥቂቱ የተጠቁሱትንና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ
ያለው የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በአሁኑ ጊዜ በወገኖቻችን ላይ የሚያካሄደው ትዕቢት፣ ማንአለብኝነት፣ ንቀትና ጭካኔ
የተሞላበት ተግባር በማውገዝ የሚከተለውን ባለአምስት ነጥብ የጋራ ዉሳኔ አስተላልፈናል።
1. የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት የዜጎች ሕገ መንግስታዊና ሰብኣዊ መብት በመጣስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በተለይም በቅርቡ
በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው ሽበራ፣ የአካል ጥቃት፣ ማፈናቀልና የስነ ልቦና ዘመቻ ይቅርና ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል
መንግስት የባዕድ ወራሪም ቢሆን የማይፈፅመው ተግባር ነው። በመሆኑም ይህ ዓይነቱ ኢሰብኣዊ እርምጃ እያወገዝን
ድርጊቱም በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
2. ሕገ መንግስት የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው በሰላማዊ መንገድ ለነፃነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰብኣዊ መብትና ለእምነት ነፃነት
መከበር ስለጠየቁ ብቻ ሰበብ አስባብ ተፈልጎባቸው በሽብርተኝነት ስም በግፍ ታስረው፣ ፍትሕ ተነፍገው አለ አግባብ በእስር
ቤት የሚማቁቁትን እነ እንስክንድር ነጋ፣ አንዱ ኣለም አራጌ፣ ርእዮት ዓለሙና ሌሎች የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ
እንጠይቃለን። እንዲሁም በአንዳንድ ክልሎች የዘር ሐረጋቸውንና ማንነታቸውን እየታየ ወገኖቻችንን ያለ አግባብ ከቤት
ንብረታቸው በማፈናቀል ሜዳ ላይ እንዲጣሉ ማድረግ ሕገ ወጥ ሥራ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያዊነት ባህልም የሚያበላሽ
ተግባር ስለሆነ ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
3. መንግስት በሀይማኖት ላይ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት በወንድማማች ህዝብ መካከል አለመተማመን፣ አላስፈላጊ ግጭትና
ትርምስ እንዲኖር ለማድረግ የሚፈበርከው የውሸት ድራማ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስውር አይደለም። በመሆኑም ህዝባችን
መንግስት በየጊዜው በሚጭረው እሳትና በሚሸርበው ተንኰል ላይ ሳይበገር የሚያሳየው ትዕግስት፣ ፍቅርና አስተዋይነት
እጅግ እናደንቃለን። መንግስት ሽብርተኝነትን እንደ ሽፋንና ወገኖችን የማጥቂያ መሳሪያነት በመጠቀም በሙስሊም ወገኖቻችን
ላይ እየወሰደ ያለው የጥቃት፣ የእስርና የድብደባ እርምጃም ሕገ ወጥና መሰረት የሌለው በመሆኑ ድርጊቱን እያወገዝን ያለ
አግባብ የታሰሩትን ወገኖቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ አበክረን እንጠይቃለን።
4. የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በንፁኃን ዜጎቻችን ላይ እያካሄደ ያለው መረኑ የለቀቀ ጥቃት በጉልበቱ ስለሚተማመን ብቻ
አይደለም። እኛ ራሳችን ሀገርንና ህዝብን ያህል ትልቅ ጉዳይ አደጋ ላይ ወድቆ እያለ በትናንሽና መለስተኛ ጉዳዮች ተጠምደን
ለአገዛዙ የተመቸን ሆነን በመገኘታችንም ጭምር ነው። ስለሆነም የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት እየፈፀመ ያለው ሕገ ወጥ
ድርጊት ይበቃ ዘንድ የጋራ ድምፃችንን እንድናሰማ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እኛም በጋራ የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ዙሪያ
ከማንም ሀገር ወዳድ ወገን ጋር አብረን ለመስራትና የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታችንን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ
እንወዳለን።
5. በሀገር ቤት ውስጥ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ የቆማችሁ ታጋይ ወገኖቻችን ሁሉ በገዢው ፓርቲ የሚፈፀምባችሁን ተፅዕኖና
መሰናክል ሳይበግራችሁ የአላማ ፅናት አንግባችሁ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ በመታገል ላይ የሞትገኙ ጀግኖቻችን ያለንን
አድናቆት እየገለፅን ከጎናችሁ የምንቆም መሆናችንን በኩራት እናረጋግጥላችኋለን። የገዢው ፓርቲ አረሜናዊ ተግባር እየባሰ
በሄደ ቁጥር የራሱን ዕድሜ እያጠረ እንዲሄድ ያደርገዋል እንጂ ጭቆናና አፈና እስካለ ድረስ ትግል የማይቆም የታመቀ እሳተ
ጎመራ መሆኑን አምባ ገነኖች ሊገነዘቡት ይገባል እንላለን። ያለንበት ዘመን ዲክታተሪያዊ ስርዓት እየከሰመ የለውጥ ውጋገን
ደግሞ እየፈነጠቀ ባለበት ወቅት ዲሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ ነፃነትና ሰላም የጠማውና ሰብኣዊ መብቱ የተነጠቀ ህዝብ በመሳሪያ
ጋጋታ፣ በሽብርና በረሃብ አንበርክኬ እገዛለሁ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar