Sider

fredag 18. januar 2013

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ… ከዛም እኔም ደስ ይበለኝ


ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ… ከዛም እኔም ደስ ይበለኝ

ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ፤ ዛሬ አስቸኳይ ጉዳይ ገጠመኝና የደቡብ ልጆች በኬኒያ የሚለውን ጨዋታ ሳልቀጥልልዎ ልቀር ነው። በምትኩ የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕረዘዳንት የአሁኑ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሆኑት አቶ ሃይለማሪያም አንድ ደብዳቤ አዘጋጅቻለሁ… እማኝ ይሆኑኛል አብረዋቸው ያንብቡልኝ!
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፤
በመጀመሪያ ሰላም ልበልዎ መሰለኝ፤ እንዴት አሉልኝ! ቀጥሎም ልጠይቅዎ መሰለኝ፤ ያንን ሃይማኖተኝነትዎን ተዉት ወይስ እንዳለ ነው? ባለፈው ግዜ በፓርላማው “እግዜር ኢትዮጵያን ይባርክ” ሲባል ከፓርላማ አባላቱ ጋር ሆነው ከት ብለው ሲስቁ አይቼዎታለሁ…? ወይስ አላየዎትም? የሆነው ይሁንና፤ ቢያንስ ግን የፓርላማ አባላቱን በምግባራቸው ሲገስፁ ባለማየቴ ነው ሃይማኖተኝነቱን ትተውት ይሆን…? ብዬ መጠራጠሬ፤ ግድየለም አለተዉትም በሚለው ታሳቢ አድርጌ ልቀጥል፤
እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረስዎ! እንዲሁም በየሱስ ስም ቀልብዎን አሰባስበው ያንቡብልኝ፤
ያኔ የስልጣኑ በር ላይ ቆመው የሀገሪቱ ጠቅላይ የመሆን አለመሆንዎ ነገር እንደ አጓጊ ትያትር ልብ ሰቀላ ላይ ሳለ፤ ከተለያዩ ቦታዎች እርስዎ ቀጣዩ ጠቅላይ የመሆን እድል እንዳልዎት ፍንጭ በሰማን ቁጥር፤ ነግሰው በፍንጭትዎ ፈገግ ሲሉልን እየታየን “ወፌ ቆመች ባልወደቀች…” እያልን ደጋፊዎ ሆነን የቆየን እጅግ በርካቶች ነን።
ለዚህ በርካታ ምክንያቶች አሉን፤ ከምክንያቶቻችን ውስጥም፤ ታጋዮቹ ደማቸው ቶሎ ቶሎ ግንፍል እያለ ፓርላማ ውስጥ ቁጣቸው አሰልችቶን ነበርና ቢያንስ እኒህ የሀይማኖት ሰው ሰከን ብለው ሲናገሩ እንሰማቸው ይሆናል። የሚለው አንዱ ነበር። ሌለውስ…? ሌላው ደግሞ አሁንም ከዕምነትዎ አንፃር መዋሸት እንደነውር ይቆጠራልና እንደቀድሞዎቹ… የምናውቀውን ሀቅ ሲዋሹን አናይም ከሚል ተስፋም ነበር። ሌላስ…? ሌላማ እንግዲህ እርስዎም እንደቀድሞዎቹ “ፈሪሳውያን” በርባን ይፈታ ክርስቶስ ይሰቀል የሚሉ አይደሉምና ንፁሀንን ለሞትና ለእስር አይንዎ እያየ አሳልፈው አይሰጡም በሚል ተስፋም ነበር።
ከነበር በኋላ፤
በዛንም ቀን አነሆ እርስዎ የተከበሩት፤ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በተቀበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። መጀመሪያ ደስ አለን ቀጥሎም ደስታችን ከምን የተነሳ ነበር…? ብለን ጠየቅን።
ቆይማ ደረቅ አደረኩብዎ መሰል… ትንሽ ዋዛ እንጨምርበት፤ ለመሳቅ ይዘጋጁ በእርስዎ ላይ የተቀለደች አንዲት ቀልድ ናት፤ አዲስ መስመር ይውረዱና ያገኟታል። (በቅንፍም አይዝዎት አዲስ መስመር ይውረዱ ነው ያልኩዎ ከስልጣንዎ ይውረዱ አላልኩም።)
በአንዱ ቀን አሉ ከሶስቱ ልጆችዎ አንዷ ኩርፍ ብላ ሳሎን ተቀምጣ አገኟት፤ ታድያ እርሶ ሆዬ በአባት አይንዎ እያዩ እና አናቷን ዳበስ ዳበስ እያደረጉ “ምን ሆነሻል ልጄ!?” ሲሉ ጠየቋት። እርሷም ለንቦጯን ጣል አድርጋ የፈተና ውጤቷ ጥሩ እንዳልሆነ ነገረችዎ፤ ይሄኔ እርስዎ ሆዬ “አይዞሽ ያገኘሽው የስራሽን ውጤት ስለሆነ አትከፊ” አሏት፤ እርሷ ግን “የሚያናድደውኮ እሱ ነው!” አለችዎ። ለካስ ልጅዎ ፈተናዋን የወደቀችው ከሰው ኮርጃ ሰርታ ኖሯል። ይሄኔ እርስዎ ሆዬ ሊመክሩ… መቼም ምክር ቀላል ነውና፤ “ልጄ የሰው ነገርማ መኮረጅ አይገባም…” ብለው ገና  ሲጀምሩላት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእርስዎ ንግግር ሲጀምር እኩል ሆነ፤ “መረጃ አለን ማስረጃ ግን የለንም…” ብለው ልክ እንደ ሟቹ ሲናገሩ ተሰማ፤ ይቺን ንግግር አቶ መለስ ፈጠሯት፤ ከዛ ሰው ለሰው ድራማ ኮረጃት፤ ከዛ ደግሞ እርስዎ ኮረጇት… ልጅዎ ይሄንን ሁሉ አየች ሳቀችም። ከዛ ስለኩረጃ አስከፊነት እንዴት ይምከሯት…!
ቀልዷ አላሳቀችዎትም መሰል። አዎ ዋናው ቁምነገሯ ማሳቁ ላይ ሳይሆን በኩረጃዎ ቤተሰብዎም መሳቀቁን ለመጠቆም ነው።
እናልዎ ስንት ተስፋ ያደረግንብዎ ሰውዬ ከውሃ አጠጣጥዎ ጀምሮ እስከ ኩስትሪያዎ እና ቁጣዎ ድረስ ቁርጥ ያለፉትን ሆነው ቁጭ! እኛም፤ ለመሆኑ ቪዲዮውን ስንት ግዜ ቢያዩት ነው!? ብለን ተደነቅን፤ ተደንቀንም ፃፍን፤
በነገራችን ላይ በዚህ የፓርላማ ውሎዎ ላይ ከብቸኛው ተቃዋሚ ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ ስለ ማተሚያ ቤት ተጠይቀው የመለሱት መልስ አስደምሞኛል። እዝችው ላይ ነገርን ነገር ያንሳውና “በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ማተሚያ ቤቶች 34 ይመስሉኝ ነበር ለካስ ከሁለት መቶ በላይ ማተሚያ ቤቶች አሉ…” ብለው ገና መልስዎ ሲጀምሩ ድሮውንም ስለሚመሯት ሀገር ያልዎት ዕውቀት አናሳ መሆኑን “አስፎገሩ” ለዚህም ነው ይህንን ንግግርዎን ኢቲቪ ማታ ድጋሚ ሲያቀርበው በሳንሱር መቀሱ ቆርጦ ያወጣው።
ለነገሩ እርስዎ ስለሀገርዎ ጉዳይ ባዳ እንደሆኑ ካወቅን ቆየን፤ ምነው እንኳ ባለፈው ጊዜ ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ “ኤርትራ የሚወስደኝ ባገኝ ሄጄ ከአቶ ኢሳያስ ጋር እታረቅ ነበር” ብለው ሲሉ፣ ጋዜጠኛይቱ፤ “ታድያ የዚህ የዚህ እግር ኳስ ቡድናችሁ ሰሞኑን ኤርትራ ሄዶ እንዳይጫወት ለምን ከለከላችሁ?” ብላ ብትጠይቅዎ “ይሄንን ገና ካንቺ ሰማሁ” ብለው ብንሰማ እኛ ለርስዎ ተሸማቀን፣ ተሸማቀን ሸማቂ መሆን አልነበር እንዴ የተመኘነው…!?
የኔ ነገር፤ የጀመርኩትን ወሬ ሳልቋጭ ሌላ ጨዋታ ውስጥ ዶልኩዎ አይደል፤ ይቅርታ ያድርጉልኝ፤ እኔስ ከአንዱ ጨዋታ ወደሌላ ጨዋታ ነው የዶልኩዎ አንዳንዶች አሉ ከችግር ወደ ችግር የሚዶሉ፤ እነርሱን ነው መገሰፅ! ታድያ ስም አልጠቀስኩም…
እናልዎ ታድያ “ማተሚያ ቤቶችን የኢህአዴግ ካድሬ ደውሎ በፍፁም አያስፈራራም” ብለው አፍዎን ሞልተው ሲናገሩ ብሰማ እኔ አፍሬ አፌን ያዝኩልዎ…
ይሄ መልስዎ ከምን ጋር ይመሳሰላል መሰልዎ አንዳንድ እናቶች አሉ ልጆቻቸውን የተንከባከቡ መስሏቸው ለባሰ ጥፋት የሚያጋልጧቸው። እንዲህ አይነት እናቶች ስለ ልጃቸው ጥፋት ስሞታ ቢመጣላቸውም “የኔ ልጅ በፍፁም እንዲህ አያደርግም” ይላሉ። ይሄ አይነቱ ምላሽ ልጆቹን የባሰ አጥፊ እነዲሆኑ ነው የሚያደርጋቸው። እንዲህ አይነት እናትና ልጆች በየሰፈሩ አሉ፤ እርስዎም ሰፈር አይጠፉም። (የድሮ ሰፈርዎ ማለቴ ነው)
ታድያ እርስዎም እዲህ እንዳሉት እናቶች “የኔ ካድሬ በፍፁም እንዲህ አያደርግም ይሉልኛል” እኔ አለሁ አይደል እንዴ ያልሞትኩ እማኝ፤
በአንድ ወቅት አንድ መፅሀፍ ላሳትም ፈልጌ ላንቻ አካባቢ ያለ አንድ ማተሚያ ቤት ሄጄ ነበር። ቀብድ ከከፈልኩት በኋላ መፅሐፌን ማተም ሊጀምር ሲል ሽፋኑን ተመለከተው። በሽፋኑ ላይ የአራት ሰዎች ፎቶግራፍ ይታያል። የዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ፣ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የምንም አቶ ልደቱ አያሌው ፎቶግራፍ ነበረበት።
እና አታሚዬ እነዚህን ፎቶግራፎች ብቻ ተመልክቶ የሰጠሁትን አስራ ምናምን ሺህ ብር ቀብድ መለሰልኝ፤ ከዛም፤ “እኔ በእሳት አልጫወትም ሰዎቹ አስጠንቅቀውኛል ውሰድልኝ” አለኝ። “በእሳት አልጫወትም” ያለው እናንተን መሆኑ ነው። በወቅቱ መንግስታችን ፀሐይ እንጂ እሳት እንዴት ይባላል ብዬ ቅር ብሎኝ ነበር። አሁን ግን እርስዎም ደጋግመው ሲናገሩ እንደሰማሁት፤ ማንኛውም ሰዉ መንግስትን አንድ ጥያቄ ሲጠይቅ “ይሄ በእሳት መጫወት ነው” ሲሉ ብሰማ እውነትም መንግስቴ እሳት ነውና እውነትም ይፋጃልና! ስል ዕውቀቴን አዳብሬያለሁ።
የሆነው ሆኖ አቶ ሃይለማሪያም ተስፋ የጣልንብዎትን ያህል ተስፋ እያስቆረጡን ነው።
ዛሬ ይሄንን ደብዳቤ እንድፅፍልዎ ያስገደደኝ ዋናው ምክንያት፤ ሰሞኑን በፌስ ቡክ ላይ አጭር መልዕክት ሰድጄልዎ ምንም ምላሽ በማጣቴ እስቲ ደግሞ ዘርዘር አድርጌ ልንገራቸው ብዬ ነው።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፤
አሁን በቅርቡ ሁለት ህፃናት ልጆች በታጠቁ የፖሊስ ሀይሎች ተገድለዋል። ይሄ የምነግርዎት ታሪክ ጋዛ ውስጥ በሮኬት ጥቃት የሆነውን አይደለም። እኛው ሀገር ኢትዮጵያችን ውስጥ ነው። ሮኬት በሆኑ ፖሊሶችዎ የተደረገ እንጂ፤
አንዷ ጡት ጠብታ ያልጨተረሰች ህፃን በእናቷ ጀርባ እንደታዘለች አዲሳባ ውስጥ “ቤታችን ፈረሰ” ብለው ለመንግስት አቤት ሲሉ በፖሊስ ዱላ ተመታ መገደሏን ሰምተን ሀዘኑ ከልባችን ሳይወጣ፤ ሌላው የሰባት አመት ህፃን ደግሞ በሀረር ከተማ ያለምንም ሰሚ አንድ አመቱን የደፈነው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ላይ በአጋጣሚ በመገኘቱ ተገደለ። ምናልባት ይህንን አልሰሙ ይሆናል።
በሀገሪቱ ውስጥ ስንት ማተሚያ ቤት እንዳለ የማያውቁ ሰውዬ፣ የሀገርዎ ብሄራዊ ቡድን ኤርትራ ሄዶ እንዳይጫወት መከልከሉን ከውጪ ጋዜጠኛ የሚሰሙ ሰውዬ፣ ይሄንን ጉዳይ እስካሁን አልሰማሁም ነበር፤ ቢሉኝ አይገርመኝም። አሁን ግን ይስሙኝ…
ባለፈው ግዜ በፌስ ቡክ ገፄ ላይ እንዳልኩዎ ይህ አይነቱ ጭካኔ የሄሮዶስ ወታደሮች ብቻ ናቸው ያደረጉት።
ወቅቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወለዳል እርሱም የአለም ሁሉ ንጉስ ይሆናል ተብሎ ትንቢት የተነገረበት ወቅት ነበር። ታድያ ሄሮዶስ በዚች ምድር ላይማ እኔ እያለሁ ማንም አይነግሳትም ብሎ በዛን ወቅት የተወለዱ ህፃናትን በሙሉ አስጨፈጨፈ። ቁጥራቸውም ሶስት ሺህ ይደርስ ነበር።
በነገራችን ላይ በሀረር ከተማ ለተገደለው ህፃን አስከሬን ለመውሰድ እናቲቱ ሶስት ሺህ ብር ክፈይ ተብላለች አሉ።
እናም ራሄል ስለ ልጆቿ አለቀሰች ልቅሶዋም በሰማይ ተሰማ!
ይላል እያነበቡ ያደጉት መፅሐፍ።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ በየሱስ ስም፤ ዛሬ ነገ ሳይሉ ይህ አይነቱን ጥቃት ያስቁሙ። እንዲሁም ይህንን የፈፀሙ ሰዎች ቅጣታቸው ሲፈፀም ያሳዩን ይህንን ማስፈፀም ከተሳንዎ ፍፃሜዎ ቢሆን ይሻልዎታል።
አክባሪዎ!

ለንደን ደነገጠች

2 ሰዎች ሞቱ
9 ሰዎች ተጎዱ
1 ሰው ክፉኛ ተጎድቷል
ዛሬ በመሀል ለንደን ከተማ ባጋጠመ

 ኢሊኮፍተር አደጋ ለንደን ከተማ ደነገጠች። ነገር ግን የኢሊኮፍተሩ አደጋ ሊያደርስ ከሚችለው ያነሰ አደጋ በመድረሱ ከተማይቱ እድለኛ ነበረች ማለት ይቻላል።
አደጋው በደረሰበት አካባቢ ትልቅ የባቡር ጣቢያ ትልልቅ ህንፃዎች እና በርካታ የህዝብ እንቅስቃሴ የሚገኝበት ነበር። ነገር ግን አንድም በፓይለቱ ብቃት አንድም ጠዋት በመሆኑ አንድም እግዜር ሲጠብቃት የደረሰው ጉዳት ሰዎች ሞት 9 ሰዎች ጉዳት እና የአንድ ሰው በጠና መጎዳት ብቻ ነው።
የተከሰተውን አደጋ ለመቆጣጠር ስድሳ የሚሆኑ የእሳት አደጋ መኪኖች እና በርካታ ፖሊሶች ተሰማርተዋል።
በእውኑ ከላይ ኢሊኮፍተሩ ሲወርድ የላይኛውም አብሮት ነበር እንጂ ከዚህ የባሰ አሰቃቂ አደጋ ሊከሰት ይችል እንደነበር። በርካቶች ተናግረዋል

የሰሜን አሜሪካና የአውሮፓ የአረና ደጋፊዎች መግለጫ አወጡ፤ “የትግራይ ሕዝብ ከሕወሓት ውጭ ሌላ አማራጭ አለው” አሉ




በሰሜን አሜሪካና በአውሮጳ የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዓረና-መድረክ ደጋፊዎች በሀገራችን ያለው አደገኛ አዝማሚያና
ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በፈረንጆች አቆጣጠር ጃንዋሪ 13/2013ዓ.ም ለ4  ሰዓታት ያህል የፈጀ የተሌ ኮንፈረስ ስብሰባ
አድርጓል። በተካሄደው ስብሰባ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎቻችን ላይ እያደረሰ ያለው የሰብኣዊ መብት
ጥሰት፣ እንግልት፣ ወከባና እስር በመሳሰሉት አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው ተወያይቷል። በውይይቱ መደምደምያም
ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ ለገዢው ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው፣ ለፍትሕና ለሰብኣዊ መብት የቆሙ ዓለም አቀፍ
ተቋማትና ታጋይ ሀይሎች፣ ለሀይማኖትና ሲቪክ ማሕበራት፣ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚከተለውን የጋራ
መግለጫና ውሳኔ አስተላልፈዋል።
 ኢትዮጵያ በህወሓት/ኢሕአዴግ በአንድ ፈላጭ ቆራጭ ቡድናዊ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት ቀን ጀምሮ እኖሆ ሁለት አሰርተ
ዓመታት አስቆጥራለች። ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ሲወጣ ካለፈው የተሻለ የዲሞክራሲ ለውጥ ይመጣል የሚል በብዙ ሰዎች ዘንድ
የተስፋ ጭላንጭል ተጥሎለት ቢኖርም “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በኋላ ግን ተስፋ የተጣለለትን
ዲሞክራሲ ደብዛውን በማጥፋት “ከፋፍለህ፣ በሆዱ ይዘህ፣ አሸብረህ፣ አደናግረህ፣ አናቁረህና አደንዝዘህ ግዛ” የሚለውን ሌሎች
ዲክታተራዊያን መንግስታት የሚከተሉትን የጡንቻ አገዛዝ ዘይቤ የዲሞክራሲ ሽፋን በመስጠት ዘላለማዊ ስልጣናቸውን
ለማጠናክር ሲሉ በበለጠ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል።
ዛሬ ከቀደሞ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላም እሳቸው የተከሉትን ጨቋኝ ስርዓትና የአፈና መዋቀር እንዳለ
በመከተል በእግዚሄር ፍቃድ ያረፉትን መሪ የሳቸው ሞት ሌሎች ተቋዋሚ ድርጅቶች ዋጋ  እየከፈሉበት ይገኛሉ። በተለይም
ላለፉት 40 ዓመታት በህወሓት ሞኖፓላዊ አገዛዝ ስር ወድቆ በሆስቴጅ (ጅሆ) ተይዞ በሻዕቢያና በህወሓት መካከል አጣብቕኝ
ውስጥ ገብቶ በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኘው የትግራይ ህዝብ ከወትሮው በባሰ መልኩ የአቶ መለስ ዕረፍት ዕዳ ከፋይና ሰለባ
ተቀባይ ሆኖ ይገኛል። ሰሞኑን በተለያየ ሚዲያ ሲገለፅ እንደሰነበተ ሁሉ ከራያ እስከ ሁመራ ድረስ በተለይም “በዓረና መደረክ”
አባላት ላይ በማነጣጠር በማሰር፣ በማስፈራራት፣ ፅሕፈት ቤታቸውን በመዝጋትና በመዝረፍ፣ ልሳናቸውን በመንጠቅና የተለያየ
መሰናክል በመፍጠር ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ከፍተኛ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የህወሓት መሪዎች የራሳቸው የግል የጓሮ ንብረት አድርገው የሚቆጣጠሩትን የትግራይ ህዝብ “ቢቸግረውም ከኛ አልፎ አቤት
የሚልበት ሌላ አማራጭ መንገድ የለውም፣ ወደደም ጠላም ከኛ ቁጥጥር አያልፍም” በሚል ንቀትና ትዕቢት የተነሳ ፓለቲካዊ
መብቱ ብቻ ሳይሆን የግል ስብእናውን፣ ማህበራዊ ፋብሪኩንና ቤት ንብረቱንም ጭምር  በግፍ እያፈራረሱት ይገኛሉ። ሰሞኑን
እንደተገለፀው በራያ አላማጣ ከተማ፣ በሁመራና በሌሎች የትግራይ ከተሞች የሚገኙ ወገኖቻችን ቤታቸው እየተናደና እየተፈናቀሉ
ይገኛሉ።
በዜጎች ላይ የሚፈፀመው የሰብኣዊ መብት ጥሰትና መፈናቀል በትግራይ ህዝብ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በሌሎች ክፍላተ
ሀገርም ተመሳሳይ ግፍ እየተፈፀመ ይገኛል። የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በትግራይ  ላይ የጀመረውን ዘመቻ በማሀል ሀገርም
በመቀጠል በሌሎች የመድረክ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በሽብርተኝነት ስም ማሰር መደብደብና ማንገላታት አሁንም በሰፊው ስራየ
ብለው ተያይዘውታል። ከዚህም አልፈው በሀይማኖት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጣልቃ በመግባት በምእመናን ወገኖቻችን
ላይ እየተካሄደ ያለው የከፋፍለህና አናቁረህ ግዛ እርምጃ እየተባባሰ መምጣቱ ለብዙ ዜጎች አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ይገኛል።    
                         የተከበራችሁ                                                  የተከበራችሁ  ውድ  ውድ  ውድውድ ኢትዮጵያውያን  ኢትዮጵያውያን  ሆይ  ሆይ!! ሆይሆይ!!  !!!!
 
የህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያላቸው የንቀትና የማንአለብኝነት ድርጊት በሰብኣዊ መብት ጥሰት ብቻ
የተወሰነ አይደለም። በሉዓላዊነታችን ላይ እየተዶለተ ያለው ሴራም በሀገራችን ላይ ያንጃበበ አደጋ መሆኑን ልብ ልነው ይገባል።
በተለይም በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመን ድብቅ አጀንዳ ሆኖ በሚስጢር ይሰራበት የነበረ ጉዳይ አሁን በነ በረከት ስምዖን ጋሃድ እየሆነ
መጥቷል። አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ በኤርትራውያን መድረክ ላይ ተገኝቶ የዳር ድንበርንና ባድመን በሚመለከት ተጠይቆ
“ባድመ በሕግ ለኤርትራ የተሰጠ ስለሆነ ውሳኔው ቀደም ሲልም ተቀብለናል። ለወደፊትም የኛ ያልሆነውን መሬት የኛ ነው ብለን
መከራከር አንችልም። በሕግ አኳያም ተገቢ አይደለም። ስለዚህ ባድመ የኤርትራ መሬት መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ
በማለት ሲገልፅ ስለ ባህር በር በሚመለከት ደግሞ የወደብ ጥያቄ የድሮ ህልመኞች (ኦልድ ስኩል) የሚያነሱት አጀንዳ እንጂ በዚሁ
ሰላሳ ዓመት ውስጥ ተወልዶ ያደገ ወጣት ኢትዮጵያዊ ጥያቄውም ጉዳዩም አይደለም ረስቶታል” ብለዋል። አቶ በረከት ንግግሩን
በመቀጠል “ቀድምም ቢሆን ከኤርትራ ጋር ወደ አላስፈላጊ ግጭትና ደም መፋሰስ እንድንገባ የገፋፉንና ኤርትራውያንን ከኢትዮጵያ
እንዲባረሩ ያነሳሱት ትምክህትና ጦረኛ አመለካከት ያላቸው እነ አቶ ገብሩ አስራትና እነ አቶ ስየ አብርሃ ናቸው እንጂ የኛ አካሄድና

አቋም ከመጀመሪያውም ግልፅ ነው። አሁንም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ኖርማላይዘሽን እንዲኖር እየሰራን ስለሆነ በቅርብ ጊዜ
እውን እንደሚሆን አረጋግጥላችኋለሁ” ሲል  በልበ ሙሉነት ሲናገር ተሰምቷል።
 በኛ አመለካከት በኢትዮጵያና በኤርትራ ወንድማማች ህዝብ መካከል በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዘላቂ ግንኙነት እንዲኖር
ከገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ መሪዎች በላይ የምንመኘውና የምናምንበትም ጉዳይ ነው። በዳር ድንበር ዙሪያ የተፈጠረው ችግርም
ሊፈታ የሚችለው ህዝብ ያልወከላቸው ከሕግ በላይ የሆኑት ጥቂት አምባ ገነን መሪዎች በጓሮ በር በሚያደርጉት የፓለቲካ ቁማር
ጫዋታና ሕገ ወጥ ሽኩት ሳይሆነ የሁለቱን ህዝቦች ይሁንታ ታክሎበት ዘላቂ ሰላምና  መልካም ጉርብትና በሚያመጣ መልኩ
ሕጋዊና ርትኣዊ መድረክ ሲፈጠር ብቻ ነው የሚል ፅኑ እምነት አለን። ነገር ግን የአቶ በረከት አነጋገር ባንድ በኩል ለሰላም የቆመና
ለኤርትራ ልዩ ተቆርቋሪ በመምሰል ሌላውን በመወንጀል ከደሙ ንፁህ ነኝ የሚል ጲላጦስ ሆኖ ለመቅረብና ለመመፃደቅ ሞክሯል።
በሌላ መልኩ ደግሞ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ለሉዓላዊነታቸው የከፈሉትን አኩሪ መስዋእትነት ደማቸውና አጥንታቸው
ገና ሳይደርቅ፣ እንዲሁም በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በየጊዜው በሻዕቢያ ታጣቂዎች እየታደኑና እየታፈኑ የሚወሰዱት ዜጎቻችን
ጥብቅና የሚቆምላቸው መንግስት አጥተው የት እንደደረሱ ሳያስጨንቀው ብድግ ብሎ ብሄራዊ ጥቅማችንን የሚነካ በጥቁር ገበያ
ማሻሻጫና ለግል ዝና መጠቀሚያ ለማድረግ መሞኮር ወንጀል ከመሆኑም በላይ ሌላ ጦርነት የሚቀሰቅስና የኢትዮጵያ ህዝብ ቁስል
የሚነካ ፀብ አጫሪ ድርጊት እንደሆነ አሁንም ልብ ልንለው ይገባል እንላለን።
እነዚህንና ሌሎች አዝማሚያዎች በአንክሮ ስንመለከትም እውነት ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው? ባለቤትዋስ ማን ነው?
የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ አድርጎናል። በመሆኑም እኛ በዲያስፓራ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውራጳና በሌሎች አህጉርራት የምንገኝ
የዓረና መድረክ ደጋፊዎች ከላይ በጥቂቱ የተጠቁሱትንና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ
ያለው የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በአሁኑ ጊዜ በወገኖቻችን ላይ የሚያካሄደው ትዕቢት፣ ማንአለብኝነት፣ ንቀትና ጭካኔ
የተሞላበት ተግባር በማውገዝ የሚከተለውን ባለአምስት ነጥብ የጋራ ዉሳኔ አስተላልፈናል።
1. የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት የዜጎች ሕገ መንግስታዊና ሰብኣዊ መብት በመጣስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በተለይም በቅርቡ
በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው ሽበራ፣ የአካል ጥቃት፣ ማፈናቀልና የስነ ልቦና ዘመቻ ይቅርና ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል
መንግስት የባዕድ ወራሪም ቢሆን የማይፈፅመው ተግባር ነው። በመሆኑም ይህ ዓይነቱ  ኢሰብኣዊ እርምጃ እያወገዝን
ድርጊቱም በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
2. ሕገ መንግስት የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው በሰላማዊ መንገድ ለነፃነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰብኣዊ መብትና ለእምነት ነፃነት
መከበር ስለጠየቁ ብቻ ሰበብ አስባብ ተፈልጎባቸው በሽብርተኝነት ስም በግፍ ታስረው፣ ፍትሕ ተነፍገው አለ አግባብ በእስር
ቤት የሚማቁቁትን እነ እንስክንድር ነጋ፣ አንዱ ኣለም አራጌ፣ ርእዮት ዓለሙና ሌሎች የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ
እንጠይቃለን። እንዲሁም በአንዳንድ ክልሎች የዘር ሐረጋቸውንና ማንነታቸውን እየታየ ወገኖቻችንን ያለ አግባብ ከቤት
ንብረታቸው በማፈናቀል ሜዳ ላይ እንዲጣሉ ማድረግ ሕገ ወጥ ሥራ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያዊነት ባህልም የሚያበላሽ
ተግባር ስለሆነ ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።
3. መንግስት በሀይማኖት ላይ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት በወንድማማች ህዝብ መካከል አለመተማመን፣ አላስፈላጊ ግጭትና
ትርምስ እንዲኖር ለማድረግ የሚፈበርከው የውሸት ድራማ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስውር አይደለም። በመሆኑም ህዝባችን
መንግስት በየጊዜው በሚጭረው እሳትና በሚሸርበው ተንኰል ላይ ሳይበገር የሚያሳየው  ትዕግስት፣ ፍቅርና አስተዋይነት
እጅግ እናደንቃለን። መንግስት ሽብርተኝነትን እንደ ሽፋንና ወገኖችን የማጥቂያ መሳሪያነት በመጠቀም በሙስሊም ወገኖቻችን
ላይ እየወሰደ ያለው የጥቃት፣ የእስርና የድብደባ እርምጃም ሕገ ወጥና መሰረት የሌለው በመሆኑ ድርጊቱን እያወገዝን ያለ
አግባብ የታሰሩትን ወገኖቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ አበክረን እንጠይቃለን።
4. የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በንፁኃን ዜጎቻችን ላይ እያካሄደ ያለው መረኑ የለቀቀ ጥቃት በጉልበቱ ስለሚተማመን ብቻ
አይደለም። እኛ ራሳችን ሀገርንና ህዝብን ያህል ትልቅ ጉዳይ አደጋ ላይ ወድቆ እያለ በትናንሽና መለስተኛ ጉዳዮች ተጠምደን
ለአገዛዙ የተመቸን ሆነን በመገኘታችንም ጭምር ነው። ስለሆነም የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት እየፈፀመ ያለው ሕገ ወጥ
ድርጊት ይበቃ ዘንድ የጋራ ድምፃችንን እንድናሰማ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እኛም በጋራ የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ዙሪያ
ከማንም ሀገር ወዳድ ወገን ጋር አብረን ለመስራትና የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታችንን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ
እንወዳለን።
5. በሀገር ቤት ውስጥ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ የቆማችሁ ታጋይ ወገኖቻችን ሁሉ በገዢው ፓርቲ የሚፈፀምባችሁን ተፅዕኖና
መሰናክል ሳይበግራችሁ የአላማ ፅናት አንግባችሁ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ በመታገል ላይ የሞትገኙ ጀግኖቻችን ያለንን
አድናቆት እየገለፅን ከጎናችሁ የምንቆም መሆናችንን በኩራት እናረጋግጥላችኋለን። የገዢው ፓርቲ አረሜናዊ ተግባር እየባሰ
በሄደ ቁጥር የራሱን ዕድሜ እያጠረ እንዲሄድ ያደርገዋል እንጂ ጭቆናና አፈና እስካለ ድረስ ትግል የማይቆም የታመቀ እሳተ

ጎመራ መሆኑን አምባ ገነኖች ሊገነዘቡት ይገባል እንላለን። ያለንበት ዘመን ዲክታተሪያዊ ስርዓት እየከሰመ የለውጥ ውጋገን
ደግሞ እየፈነጠቀ ባለበት ወቅት ዲሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ ነፃነትና ሰላም የጠማውና ሰብኣዊ መብቱ የተነጠቀ ህዝብ በመሳሪያ
ጋጋታ፣ በሽብርና በረሃብ አንበርክኬ እገዛለሁ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው።
                 
           
                          ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ