Sider

lørdag 20. juli 2013

በቦንድ ሽያጭ ያልተሳካው የገንዘብ ዘረፋ በኮንደሚኒየም ሰበብ መሳካት የለበትም!!!

ወያኔ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በከተሞች አካባቢ ምንም አይነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሮት አያውቅም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ከተሞች በጠላትነት በተፈረጀው አማራና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች የተሞሉ ስለሆነ ነው ይላል። ዋና ከተማችን አዲስ አበባ በዚህ ውንጀላ ዋጋ ከከፈሉት ከተሞች ግንባር ቀደሟ ናት። በተለይ በመጀመሪያው የወያኔ 10 (አሥር) የሥልጣን አመታት የከተማዋን የነዋሪዎች አሰፋፈር ስብጥር ሆን ብሎ ለመቀየር ከመሞከር ጀምሮ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞችን አቅም ለማዳከም በርካታ አሳዛኝ እርምጃዎች ተወስደዋል።
ታሪክን ወደኋላ መለስ ብለን እንቃኝ። የፋሺስት ጣልያን ጦር በእንግሊዝ ጦር ትብብር በኢትዮጵያ አርበኞች ከተደመሰሰ በኋላ በአሸናፊነው ወደከተሞች የገባው የእንግሊዝ ጦር ያገኘውን ንብረት በወቅቱ የቅኝ ግዛቶቹ ወደ ነበሩት ኬንያና ሱማሌ አሽሽቷል። ከብዙ ዓስርተ ዓመታት በኋላ ወያኔ ይህንኑ እኩይ ተግባር ደገመው። ወያኔ በያዛቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘኛቸውን ውድ ዋጋና ትላልቅ ጥቅሞች የሚሰጡ በርካታ ንብረቶችን ከተለያዩ መንግሥታዊና ወታደራዊ ተቋሞች፤ ዩኒቨርስቲዎች፤ ሆስፒታሎች፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫዎች ዘርፎ እስከዛሬ ትክክለኛ አደራሻው ለሕዝብ ይፋ ወደ አልተደረገ የሰሜን አካባቢ አይናችን እያየ በረጃጅም የጭነት መኪናዎች አጓጉዞአል። በቀድሞ መንግሥት ዘመን ምንም ዕጥረት እንዳልነበረው የሚታወቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የ24 ሰዓት መብራት አገልግሎትን እንኳ ሳይቀር በማስተጓጎል የከተማውን ሕዝብ ተበቅሎአል።
ወያኔ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ጥላቻ በጥቂቱም ቢሆን ረገብ ያደረገ የሚያስመስል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጀመረው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት በቃኝ የማያውቁት የቀድሞ ተጋዳላዮች የአገሪቱን አንጡራ ሃብት እንዲበዘብዙ በተመቻቸላቸው እድል ዘርፈው የያዙትን ገንዘብ ከውልደታቸው ጀምሮ ከሚታወቁበት አካባቢ ሕዝብ እይታ አርቀው “ለደም ካሳ” በዋና ከተማችን እምብርት በነፃ በታደላቸው የከተማ ቦታዎች ላይ ህንጻዎችን በመገንባት ንብረት እንዲይዙ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መቀመጫ በሆነቺው አዲስ አበባ ምርጫ 97ን ተከትሎ ገጥሞት የነበረው ሽንፈት ባስከተለው መዘዝ የተበላሸ ገጽታውን በህንጻና መንገዶች ግንባታ ስም ለማሳመር መጣር ናቸው።
የአዲስ አበባ ኮንደሚኒዬም ቤቶቾ ግንባታ ከምርጫ 97 ቦኋላ በመኖሪያ ቤቶች እጥረት የሚሰቃየውን ሕዝብ ልብ ለማማለልና የፖለቲካ ድጋፍ ለመግዛት ያስችላል ተብሎ የታሰበ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት ድብቅ ዓላማዎችም አሉት።
  1. በዘረፋ የከበሩ የቀድሞ ተጋዳላዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አይናቸው ያረፈባቸውን ቁልፍ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች ሁሉ ለዘመናት በባለይዞታነት ይዘው የኖሩትን በልማትና በእንቨስትመንት ሥም በማፈናቀል ወደ ግላቸው ላማዞር ያስችላቸዋል፤
  2. በተለያዩ ሥም የተቋቋሙ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶቻቸው በግንባታው ሥራ በመሳተፍ መጠነ ሰፊ የሆነ ትርፍ ለማግበስበስ ያመቻቸዋል፤
  3. የሥርዓቱን ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከሌላ ቦታ አምጥቶ በማስፈር በጠላትነት የተፈረጀውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጽዕኖ ለማምከን ይረዳል፤
  4. በሀብት ዘረፋው ለመሳተፍ እድል የሌላቸው የበታች ካድሬዎችና ታማኝ አገልጋዮችን ተጠቃሚ በማድረግ በአለቆቻቸው ዘረፋ ተማረው ልባቸው እንዳይሸፍት ይከላከላል ፤
  5. ከተወለዱበትና ካደጉበት የግልና የቀበሌ ቤቶች ያለውደታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የኮኖዶሚኒየሙን ሂሳብ መክፈል እስከቻሉ ድረስ “ከቤታችን ተፈናቅለን ሜዳ ላይ ተጣልን” የሚል እሮሮ በማሰማት መንግስት ላይ አመጽ እንዳያስነሱ ስጋት ለመቀነስ ይረዳል፤
  6. ከሰሞኑ 40 ከመቶ ተብሎ በወጣው ፖሊሲ እንደታዘብነው ደግሞ ዜጎችን በማጓጓት ተቸግረው ያጠራቀሙትን ገንዘብ ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲከቱ በማድረግ የገንዘብ እጥረት አንገቱ ድረስ የዘለቀውን አገዛዝ ለመታደግ ያስችላል (በ16 የሥራ ቀናት ብቻ ከተመዘገበው 750, 000 የኮንዶሚንዬም ቤት አመልካች 750 000 000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር መሰብሰቡን ልብ ይሏል)
ከዚህም በተጨማሪ የኮንደሚኒዬም ቤቶች ግንባታ በቂ ጥናትና ዝግጅት ያልተደረገበት የይድረስ ይድረስ ሥራ መሆኑን የቤቶቹ ርክክብ በተፈጸመ ማግሥት ስለ ህንጻው መሬት ውስጥ መስጠምና መጣመም መጀመር እየወጥ ያሉ ዜገባዎች ዋቤ ምስክር ናቸው።
የወያኔ መሪዎችና ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከኮንደሚኒዬም ግንባታ በተጨማሪ ከምርጫ 97 ወዲህ ከፍተኛ ገንዘብ እያግበሰበሱ ያሉት የከተማ ቦታዎችን በውድ ዋጋ የልጅ ልጆቻቸው እንኳ ሊደርሱበት ለማይችል የግዜ ገደብ በሊዝ በመቸብቸብ ነው። በዚህ የመሬት ቅሪሚያ አንዳንድ ስግብግቦች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” እንዲሉ “ወያኔዎች መሬታችንን እየተቀራመቱ ስለሆነ ተሻምተን ማስቆም አለብን” በሚል ብልጣ ብልጥነት ከሚኖሩበት የስደት አገር እየተጓዙ የወያኔን ገቢያ በማድራት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በትዝብት ተመልክቶአል። አገርን ዘርፎ ለዘራፊ እየሰጠ ያለ መንግሥት ሴራ ተባባሪ መሆን በሞራልም ሆነ በህሊና ዳኝነት የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑ ሳያንስ እነዚህ በስግብግብነት የተጠመዱ ወገኖች ለንብረታቸው ደህንነት ሲባል ወያኔ ዓይናቸው እያየ ጆሮአቸው እየሰማ በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃዎች እንኳ ለመቃወም ድፍረት በማጣት ሌላ ትዝብት ውስጥ ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ለመሆኑ እነዚህ ወገኖች ለፍተው ባገኙት ገንዘብ የገዙት ባርነትን ነው ወይስ የንብረት ባለቤትነትን ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይኖራቸዋል?
የዜጎች መብት በተከበረበት አገር ከዜግነት መብቶች አንዱ የግል ሀብት ባለቤት ለመሆን ገደብ የሌለው ነፃነትና እድል መኖሩ ነው:: ወያኔ በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያችን ግን የንብረት ባለቤት ለመሆን የሥርዓቱ ባለሟል መሆን አለያም ከፖለቲካ ባላንጣነት መራቅ ዋና መስፈርት ናቸው። በዚህ መስፈርት ከወያኔ ጋር ተሻምተው ወይም ተሻርከው የንብረት ባለቤት ለመሆን እየተሽቀዳደሙ ያሉ ወገኖች ሊያውቁት የሚገባው ሃቅ ቢኖር አድሎአዊነት በሰፈነበት መንገድ የተገኘ ማንኛውም አይነት ሀብት ወይም ንብረት ወደፊት በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ በሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ህገዊ ጥበቃ የሚኖረው አለመሆኑን ነው። ብሄራው የአገር ጥቅም ላይ ክህደት ከፈጸመ ፤ ዜጎችን በማፈን ሰቆቃ ካደረሰ ፤ የአገሪቷን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል መሬታቸውን ቀምቶ ለሌሎች አሳልፎ ከሰጠ ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ዘርፎ ለዘራፍ ከሰጠ ወንጀለኛ መንግሥት ጉያ ውስጥ ተወሽቆ እስከ ወዲያኛው የህግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችል ንብረት ባለቤት መሆን ማሰብ እጅግ ይቸግራል። ዜጎች በራሳቸው ወዝ ለፍተው ያገኙትን ንብረት ሳይቀር በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ብቻ በሽብርተኝነት እየፈርጀ የሚነጥቅ ሥርዓት ዕድሜ እንደምንጠብቀው ረዥም ሊሆን እንደማይችል ማሰብ ብልህነት ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ አገዛዝ በውጭው ዓለም በስደት ከሚኖረው ወገናችን በአባይ ግድብ የቦንድ ሺያጭ ሥም ለመሰብሰብ ሞክሮ ያልተሳካለትን ገንዘብ በመሬት ሺያጭ እና በኮንደሚኒዬም ቤት ግዥ ሥም እንዲያገኝ ሊፈቀድለት አይገባም ብሎ ያምናል:: ስለዚህም እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ከዚህ ከኮንደሚኒዬም ቤቶች በስተጀርባ ያለውን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥ ጥረቱን በማምከን የሕዝባዊ እምብተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

EU delegation: Ethiopia should release jailed journalists and activists

ADDIS ABABA, Ethiopia — A European Union parliament delegation on Wednesday called on Ethiopia’s government to release jailed journalists and activists, but in a sign the call may not be heeded the delegation was denied from visiting a prison it had been approved to see.

The head of the delegation, Barbara Lochbihler, said Ethiopia is jailing journalists and activists for “exercising their legitimate right to freedoms of expression, association and religion.” The group is concerned by reports of misuse of the country’s anti-terrorism legislation to stifle dissent, she said.
“Despite the country’s excellent constitution, we note flaws in the impartiality of the judicial system,” Lochbihler told journalists at a press conference Wednesday.
A spokesman for the Ethiopian Prime Minister said the country doesn’t have any political prisoners and that prisoners would not be released “just because some European Union members said so.”
According to the Committee to Protect Journalists, the Ethiopian government criminalizes the coverage of any group the government deems to be a terrorist group, a list that includes opposition political parties.
“Among those jailed is Eskinder Nega, an award-winning blogger whose critical commentary on the government’s extensive use of anti-terror laws led to his own conviction on terrorism charges,” the group said in its latest survey, which placed Ethiopia among the world’s top ten worst jailers of journalists.
The EU parliament delegation said certain broadcasters are jammed in Ethiopia and that access to the Internet and social media are “regularly restricted.” The practice is at odds with the Ethiopian constitution, the delegation said in a statement.
The four-person delegation, drawn from the parliament’s subcommittee on human rights, said the Ethiopian government must guarantee freedom of speech and the right to peaceful assembly at all times in accordance with its constitution and obligations under international law. The delegation met top government officials, activists and leaders of the opposition.
Earlier on Wednesday the delegation was scheduled to visit to the country’s Kaliti prison where most activists are believed to be serving their sentence. But the prison director turned the group back on arrival, saying “he didn’t have time to work with you,” according to a member of the delegation, Jorg Leichtfried.
Leichtfried told a news conference their visit was “overshadowed” by the incident. He described it as an episode he doesn’t wish to experience again. All four delegation members spoke about the incident, which appeared to have frustrated them.
The delegation said Ethiopia itself has requested international assistance to improve its detention centers and their visit was to have a firsthand experience of the detention conditions.
Getachew Reda, a spokesman for Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, said he was not aware of any decisions either to grant permission to see the prison or to deny it. Getachew said only family members can visit the prisoners.
“We don’t have any single political prisoner in the country. We do have, like any other country, people who were convicted of crimes including terrorism who are currently serving their sentence. They would only be freed when either they complete their sentence or probation on good behavior,” Getachew told the Associated Press on Wednesday. “We are not going to do release anyone just because some European Union members said so.”
He criticized the delegation’s statement, calling it “unhelpful” to relations between Ethiopia and the EU.
The EU is one of Ethiopia’s largest donors with millions of dollar spent on development projects across the country.
Hailemariam was scheduled to meet the visiting delegation on Wednesday night.
The European lawmakers also met with African Union officials. Lochbihler criticized Nigeria and the AU for allowing Sudanese President Omar al-Bashir to travel to Abuja earlier this week. The International Criminal Court has an arrest warrant out for Bashir.
Copyright 2013 The Associated Press. All rights reserved. This material may not be published, broadcast, rewritten or redistributed.

አዜብ መስፍን ከአቶ ገ/ዋህድ፣ አቶ ነጋና ምህረተአብ ጋር በመመሳጠር በ3 መርከብ ስሚንቶ አስጭነው በማስገባት የሙስና ወንጀል መፈፀማቸውን ምንጮች አጋለጡ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገ/ዋህድ፣ አቶ ነጋና ምህረተአብ ጋር በመመሳጠር በሶስት መርከብ ስሚንቶ አስጭነው
አገር ውስጥ በማስገባት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል መፈፀማቸውን ምንጮች አጋለጡ። በተከለከለ ፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ
አገር ቤት የገባው ስሚንቶ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ትርፍ አዜብና ግብረአበሮቻቸው እንደዛቁበት ያረጋገጡት
ምንጮቹ፣ አያይዘውም ጉዳዩ በደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ እጅ እንደገባ አስታውቀዋል። በሕገወጥ መንገድ
የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ በመመደብና አስፈላጊውን ትእዛዝ በመስጠት እንዲሁም የጥቅም ተካፋይ በመሆን
ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት አዜብ መስፍን ከዚህ ድርጊታቸው በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ከስሚንቶው ጋር በተያያዘ
ተመስርቶ የነበረውን ክስ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ይህና ሌሎች ተያያዥ የወንጀል
ድርጊቶችን የሚያስረዱ ማስረጃዎች በአቶ ጌታቸው እጅ እንደገቡ አረጋግጠዋል። አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር
በኮንትሮባንድ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር ውስጥ ያስገቧቸው የህክምና መሳሪያዎች ተይዘው ክስ
ከተመሰረተባቸው በኋላ ክሱ እንዲቋረጥ ያደረጉት አዜብ መሆናቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ በተለያዩ ጊዜያት የገቡና
የነጋ ገ/እግዚያብሄር ንብረት የሆኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ያለቀረጥ እንዲገቡ በማድረግ አዜብ መተባበራቸውን
አያይዘው ገልፀዋል። ጉዳዩም «ክስ በማቋረጥ..» በሚል በሰነድ ተደግፎና ከሌሎች መሰል ድርጊቶች ጋር ተያይዞ
በታሳሪዎች ላይ ክስ የቀረበ ቢሆንም፣ ዋናው ተዋናይ ግን አዜብ ሳይጠየቁ መቅረታቸው አነጋጋሪ መሆኑን ምንጮቹ
አልሸሸጉም። ከስሚንቶው ጋር በተያያዘ አስተያየት
የጠየኳቸው ታዋቂ የሆኑ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ ፥ «
መንግስት ስለ ፍራንኮ ቫሉታ ሕግ አውጥቷል፤ ይህን
በመተላለፍ ሶስት መርከብ ስሚንቶን የሚያክል ነገር
በታሳሪዎቹ ብቻ ሊፈፀም አይችልም፤ ከዚህ ሕገወጥ ድርጊት
በስተጀርባ ትልቅና ቁልፍ ስልጣን ያለው ሰው እጁ
እንዳለበት ግልፅ ነው።» ብለዋል።
በተያያዘም ስለ ነጋ ገ/እግዚያብሄርና ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ
የጀርባ ታሪክ በተመለከተ ምንጮቹ ተከታዩን መረጃ
አስቀምጠዋል፤ “ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ
የአቶ ነጋ ስራ የመኪና ድለላና ኮረዶችን ከባለስልጣናት ጋር
የማገናኘት የድለላ ተግባር ላይ ተሰማርቶ እንደነበረ
ይገልፃሉ። በተለይ ሴቶችን እየመረጠ ለበርካታ የገዢው
ሹማምንት ለወሲብ ከማቅረብ ጎን ለጎን የሕወሐት ቁልፍ
ባለስልጣናትን በእጁ የማስገባት አጋጣሚ ፈጥሮለታል ፥
ይላሉ ምንጮቹ። ከባዶ ተነስቶ ሚሊየነር የሆነበት ምስጢሩ
አዜብ መስፍን መሆናቸውን ያሰምሩበታል። ለዚህም «ነፃ
ትሬዲንግ፣ ባሰፋና…» ሌሎች ከፍተኛ የቢዝነስ ተቋማቱና በሕገወጥ የዘረፋ ተግባር በድፍረት ተሰማርቶ መቆየቱን
ከሞላ ጎደል ይጠቅሳሉ። በባለስልጣናቱ ተረማምዶ ከአዜብ ጋር በፈጠረው <ልዩ ቁርኝት> የተገኘ ሃብት እንደሆነ
ይገልፃሉ። ከአዜብ ጋር በማሌዢያና ለንደን የፈፀሟቸው አስነዋሪ ተግባራት የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎች በደህንነት
ሃላፊው እጅ እንደገቡ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ የሁለቱን ግንኙነት በተመለከተ አብዛኛው የሕወሐት አመራር ጠንቅቆ
እንደሚያውቀው አስታውቀዋል። አቶ ነጋ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ማመን ተስኗቸው ከማንገራገራቸው ባሻገር፥
«..ለአዜብ ስልክ እንድደውል ፍቀዱልኝ?» በማለት መማፀናቸውንና ደህንነቶቹ እንዳልተቀበሏቸው ምንጮቹ
አመልክተዋል። በሌላም በኩል ከአዜብ ጋር ተመሳሳይ <ግንኙነት> ያላቸው ሌሎች ሁለት ባለሃብቶች፥ አንዱ 40
ሚሊዮን የፈጀ ባለስድስት ፎቅ የቢዝነስ ተቋም (ቦሌ ከሜጋ አጠገብ) አዜብ በለገሱት ገንዘብ እንዲገነባ ሲደረግ፣ ከዚህ
ግለሰብ ጋር በተደጋጋሚ በዱባይ በውቂያኖስ ላይ በተገነባውና የቱጃሩ አልወሊድ ቢንጣለል ንብረት በሆነው
“ኪንግደም” ባለ4 ኮከብ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል እንደተገናኙ፣ እንዲሁም ሌላኛው የአንድ ቢሊየን ብር ባለሃብት ሆኖ
ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ አዜብ ማድረጋቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የአቶ ገ/ዋህድ ማንነት በተመለከተ ምንጮቹ ይህን ይላሉ፤ « ገ/ዋህድ የኢሰፓ አባል ሆኖ በአስመራ እስከ 1982ዓ.ም
ያገለግል ነበር። በዚሁ አመት መጨረሻ በራማ በኩል አድርጎ ሕወሐትን ተቀላቀለ። በወቅቱ በመቀሌ እንዲቋቋም
በተደረገውና የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ መኮንኖች (ምርኮኛ) የተካተቱበት <ኢዴመአን> የተባለ ድርጅት መስራች አባል
ነበር – ገ/ዋህድ። በ1983 ዓ.ም የሁለት ሳምንት ወታደራዊ ስልጠና ወይም በድርጅቱ አጠራር “ተአለም” ከወሰደ
በኋላ በአጋጣሚ ፓርቲው መላ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ምንጮቹ ያመለክታሉ። በሲቪል ሰርቪስ አልፎ ደቡብን
ከጀርባ እንዲመሩ ከተመደቡት አቶ ቢተው በላይ ጋር በአዋሳ ተመደበ። በ1993ዓ.ም በተፈጠረው የፓርቲው
መሰንጠቅ አመቺ አጋጣሚ የተፈጠረለት ገ/ዋህድ የክልሉን ፕ/ት አቶ አባተ ኪሾን፣ ቢተው በላይና ሌሎችም
እንዲታሰሩ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫወተ። ለዚህ ታማኝነቱ የላቀ ቦታ በመለስ ማግኘት እንደቻለና ከዛ በኋላ
በየቀኑ ከአዜብና መለስ ጋር በስልክ ይገናኝ እንደነበረ በፈለገው ጊዜ ቤተመንግስት ይገባና ይወጣ እንደነበረ ምንጮቹ
አረጋግጠዋል። በአዜብ መልካም ፈቃድ በጉምሩክ ወሳኝ ስልጣን እንዲጨብጥ መደረጉንም አክለው ገልፀዋል።
ከአዜብና ሸሪኮቻቸው ጋር በመነጋገርና በመመሳጠር ስሚንቶና ሌሎች ቁሳቁሶች በህገወጥ መንገድ ቀረጥ
ሳይከፈልባቸው አገር ቤት እንዲገቡ በማድረግ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ገ/ዋህድ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሃብት
ከዘረፋው እንዳተረፈም ተመልክቷል። ባለቤቱ ኮ/ል ሃይማኖትም እንዲሁ አዜብ በሚመሩት የሴቶችና ፀረ-ኤድስ
ተቋም በምክትል ሃላፊነት እንዲመደቡና በየአመቱ ከአሜሪካ ብቻ እስከ 240 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ መልክ
የሚገኘውን ገንዘብ በግልፅ በመዝረፍ ተባባሪ ሆነው መቆየታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

fredag 19. juli 2013

ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ሲጋለጥ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

  • ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ሲጋለጥ
    (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
    ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገ/ዋህድ፣ አቶ ነጋና ምህረተአብ ጋር በመመሳጠር በሶስት መርከብ ስሚንቶ አስጭነው አገር ውስጥ በማስገባት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል መፈፀማቸውን ምንጮች አጋለጡ። በተከለከለ ፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ አገር ቤት የገባው ስሚንቶ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ትርፍ አዜብና ግብረአበሮቻቸው እንደዛቁበት ያረጋገጡት ምንጮቹ፣ አያይዘውም ጉዳዩ በደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ እጅ እንደገባ አስታውቀዋል። በሕገወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ በመመደብና አስፈላጊውን ትእዛዝ በመስጠት እንዲሁም የጥቅም ተካፋይ በመሆን ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱት አዜብ መስፍን ከዚህ ድርጊታቸው በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ከስሚንቶው ጋር በተያያዘ ተመስርቶ የነበረውን ክስ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ይህና ሌሎች ተያያዥ የወንጀል ድርጊቶችን የሚያስረዱ ማስረጃዎች በአቶ ጌታቸው እጅ እንደገቡ አረጋግጠዋል። አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር በኮንትሮባንድ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ አገር ውስጥ ያስገቧቸው የህክምና መሳሪያዎች ተይዘው ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ክሱ እንዲቋረጥ ያደረጉት አዜብ መሆናቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ በተለያዩ ጊዜያት የገቡና የነጋ ገ/እግዚያብሄር ንብረት የሆኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ያለቀረጥ እንዲገቡ በማድረግ አዜብ መተባበራቸውን አያይዘው ገልፀዋል። ጉዳዩም «ክስ በማቋረጥ..» በሚል በሰነድ ተደግፎና ከሌሎች መሰል ድርጊቶች ጋር ተያይዞ በታሳሪዎች ላይ ክስ የቀረበ ቢሆንም፣ ዋናው ተዋናይ ግን አዜብ ሳይጠየቁ መቅረታቸው አነጋጋሪ መሆኑን ምንጮቹ አልሸሸጉም። ከስሚንቶው ጋር በተያያዘ አስተያየት የጠየኳቸው ታዋቂ የሆኑ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ ፥ « መንግስት ስለ ፍራንኮ ቫሉታ ሕግ አውጥቷል፤ ይህን በመተላለፍ ሶስት መርከብ ስሚንቶን የሚያክል ነገር በታሳሪዎቹ ብቻ ሊፈፀም አይችልም፤ ከዚህ ሕገወጥ ድርጊት በስተጀርባ ትልቅና ቁልፍ ስልጣን ያለው ሰው እጁ እንዳለበት ግልፅ ነው።» ብለዋል።
    በተያያዘም ስለ ነጋ ገ/እግዚያብሄርና ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ የጀርባ ታሪክ በተመለከተ ምንጮቹ ተከታዩን መረጃ አስቀምጠዋል፤ “ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ የአቶ ነጋ ስራ የመኪና ድለላና ኮረዶችን ከባለስልጣናት ጋር የማገናኘት የድለላ ተግባር ላይ ተሰማርቶ እንደነበረ ይገልፃሉ። በተለይ ሴቶችን እየመረጠ ለበርካታ የገዢው ሹማምንት ለወሲብ ከማቅረብ ጎን ለጎን የሕወሐት ቁልፍ ባለስልጣናትን በእጁ የማስገባት አጋጣሚ ፈጥሮለታል ፥ ይላሉ ምንጮቹ። ከባዶ ተነስቶ ሚሊየነር የሆነበት ምስጢሩ አዜብ መስፍን መሆናቸውን ያሰምሩበታል። ለዚህም «ነፃ ትሬዲንግ፣ ባሰፋና…» ሌሎች ከፍተኛ የቢዝነስ ተቋማቱና በሕገወጥ የዘረፋ ተግባር በድፍረት ተሰማርቶ መቆየቱን ከሞላ ጎደል ይጠቅሳሉ። በባለስልጣናቱ ተረማምዶ ከአዜብ ጋር በፈጠረው <ልዩ ቁርኝት> የተገኘ ሃብት እንደሆነ ይገልፃሉ። ከአዜብ ጋር በማሌዢያና ለንደን የፈፀሟቸው አስነዋሪ ተግባራት የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎች በደህንነት ሃላፊው እጅ እንደገቡ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ የሁለቱን ግንኙነት በተመለከተ አብዛኛው የሕወሐት አመራር ጠንቅቆ እንደሚያውቀው አስታውቀዋል። አቶ ነጋ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ማመን ተስኗቸው ከማንገራገራቸው ባሻገር፥ «..ለአዜብ ስልክ እንድደውል ፍቀዱልኝ?» በማለት መማፀናቸውንና ደህንነቶቹ እንዳልተቀበሏቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በሌላም በኩል ከአዜብ ጋር ተመሳሳይ <ግንኙነት> ያላቸው ሌሎች ሁለት ባለሃብቶች፥ አንዱ 40 ሚሊዮን የፈጀ ባለስድስት ፎቅ የቢዝነስ ተቋም (ቦሌ ከሜጋ አጠገብ) አዜብ በለገሱት ገንዘብ እንዲገነባ ሲደረግ፣ ከዚህ ግለሰብ ጋር በተደጋጋሚ በዱባይ በውቂያኖስ ላይ በተገነባውና የቱጃሩ አልወሊድ ቢንጣለል ንብረት በሆነው “ኪንግደም” ባለ4 ኮከብ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል እንደተገናኙ፣ እንዲሁም ሌላኛው የአንድ ቢሊየን ብር ባለሃብት ሆኖ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ አዜብ ማድረጋቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
    የአቶ ገ/ዋህድ ማንነት በተመለከተ ምንጮቹ ይህን ይላሉ፤ « ገ/ዋህድ የኢሰፓ አባል ሆኖ በአስመራ እስከ 1982ዓ.ም ያገለግል ነበር። በዚሁ አመት መጨረሻ በራማ በኩል አድርጎ ሕወሐትን ተቀላቀለ። በወቅቱ በመቀሌ እንዲቋቋም በተደረገውና የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ መኮንኖች (ምርኮኛ) የተካተቱበት <ኢዴመአን> የተባለ ድርጅት መስራች አባል ነበር – ገ/ዋህድ። በ1983 ዓ.ም የሁለት ሳምንት ወታደራዊ ስልጠና ወይም በድርጅቱ አጠራር “ተአለም” ከወሰደ በኋላ በአጋጣሚ ፓርቲው መላ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ምንጮቹ ያመለክታሉ። በሲቪል ሰርቪስ አልፎ ደቡብን ከጀርባ እንዲመሩ ከተመደቡት አቶ ቢተው በላይ ጋር በአዋሳ ተመደበ። በ1993ዓ.ም በተፈጠረው የፓርቲው መሰንጠቅ አመቺ አጋጣሚ የተፈጠረለት ገ/ዋህድ የክልሉን ፕ/ት አቶ አባተ ኪሾን፣ ቢተው በላይና ሌሎችም እንዲታሰሩ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫወተ። ለዚህ ታማኝነቱ የላቀ ቦታ በመለስ ማግኘት እንደቻለና ከዛ በኋላ በየቀኑ ከአዜብና መለስ ጋር በስልክ ይገናኝ እንደነበረ በፈለገው ጊዜ ቤተመንግስት ይገባና ይወጣ እንደነበረ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በአዜብ መልካም ፈቃድ በጉምሩክ ወሳኝ ስልጣን እንዲጨብጥ መደረጉንም አክለው ገልፀዋል። ከአዜብና ሸሪኮቻቸው ጋር በመነጋገርና በመመሳጠር ስሚንቶና ሌሎች ቁሳቁሶች በህገወጥ መንገድ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው አገር ቤት እንዲገቡ በማድረግ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ገ/ዋህድ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሃብት ከዘረፋው እንዳተረፈም ተመልክቷል። ባለቤቱ ኮ/ል ሃይማኖትም እንዲሁ አዜብ በሚመሩት የሴቶችና ፀረ-ኤድስ ተቋም በምክትል ሃላፊነት እንዲመደቡና በየአመቱ ከአሜሪካ ብቻ እስከ 240 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ መልክ የሚገኘውን ገንዘብ በግልፅ በመዝረፍ ተባባሪ ሆነው መቆየታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።
    በማንደፍሮ መንግስቱ
https://www.facebook.com/photo.php?v=10200309772608009

tirsdag 25. juni 2013

http://www.dagbladet.no/2013/06/25/nyheter/krig_og_konflikt/utenriks/verdens_verste_land/27872885/

tirsdag 11. juni 2013

http://ethsat.com/video/esat-fundraising-program-oslo-norway-feb-2013/